በኒያ ፋዉንዴሽን እና በአጋር አካላት የተዘጋጁ ፣ በኦቲዝም ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች፣ የመንግስት አካላት ፣ ባለሙያዎች እና ወላጆች ጠቃሚ የሆኑ ሁለት የህትመት ዉጤቶች ይፋ ተደርገዋል።
የመጀመሪያ ፈታኙን የኦቲዝም ወጣቶች የስነ ተዋልዶ ጤና ጉዳዮች አስመልክቶ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል አጋዥ ማንዋል ሲሆን ሁለተኛው የቤት ለቤት እና ማህበረሰብ አቀፍ የኦቲዝም ተሃድሶ እና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል አጋዥ የሆነ ማንዋል ነው።
እነዚህ ማንዋሎች በወ/ሮ ዘሚ የኑስ የተጀመሩ ስራዎች ወደ መጠናቀቅ እንዲደርስ ያደረጉ እና በአገራችን ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣዉን የኦቲዝም ሁኔታ ላይ ድጋፍ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ መሆናቸው ተጠቁሟል።
እነዚህ አዳዲስ የማስተማሪያ ማንዋሎች (Manuals) ይፋ መደረጋቸው፣ አዲስ ከተመሰረተው የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ ዜና ጋር ተዳምሮ በዘርፉ ትልቅ እምርታ የታየበት ወቅት መሆኑን ያሳያል። በተለይም በወይዘሮ ዘሚ የኑስ የተጀመሩ ራዕዮች ፍሬ አፍርተው ለዚህ መብቃታቸው ለስራው ቀጣይነት ትልቅ ትርጉም ያለው ነው።

የእነዚህ ህትመቶች ዋና ፋይዳ፣
#የኦቲዝም ወጣቶች ስነ-ተዋልዶ ጤና አጋዥ ማንዋል፡ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ብዙ ጊዜ በማህበረሰባችን ውስጥ በግልጽ የማይወራ ቢሆንም፣ ኦቲዝም ያለባቸው ወጣቶች ለአካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ለውጦች የሚገባቸውን ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ ወሳኝ ነው። ወላጆች እና ባለሙያዎች ወጣቶቹን እንዴት ማስተማር እና መጠበቅ እንዳለባቸው ሳይንሳዊ እና ባህላዊ ሁኔታን ያገናዘበ መመሪያ ይሰጣል።

#የቤት ለቤት እና ማህበረሰብ አቀፍ ተሃድሶ ማንዋል፦ ሁሉም የኦቲዝም ህፃናት ወደ ማዕከላት የመሄድ ዕድል በማያገኙበት ሁኔታ፣ ይህ ማንዋል ድጋፉን ወደ ቤተሰብ እና መንደር ያወርደዋል።ቤተሰቦች በቤታቸው ውስጥ ልጆቻቸውን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ያግዛል፤ እንዲሁም የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች በየደረጃው ድጋፍ እንዲሰጡ አቅም ይፈጥራል።

ህትመቱን እዉን ለማድረግ ድጋፍ ያደረጉ የጊዳቦ ፖሊሲ ማዕከል፣ የፓካርድ ፋዉንዴሸን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ ባለሙዎች እና ቴክኒካል አድቫይዘሮች ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን!