ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ ምስረታ መድረክ በኢሊሌ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ለረጅም ዘመናት ስንሻው የቆዬው ሁሉንም በኦቲዝም ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች እና ማህበራት፣ ባለሙያዎች እና ቤተሰቦች እንዲሁም በጉዳዩ ፍላጎት ያላቸውን ባለድርሻ አካላት የሚያቅፍ ሀገር አቀፍ የኦቲዝም ሶሳይቲ ምስረታ እዉን ሆኗል። ሶሳይቲውን የሚመሩ 13 አባላት ያሉት የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ይህን ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ማህበር የማደራጀት ከፍተኛ ሀላፊነት በጉባኤው ተሰጥቷል።
የኢትየጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት
1. ወ/ሮ እሌኒ ዳምጠው : ከኒያ ፋዉንዴሽን
2. ወ/ሮ ትዕግስት ሀይሉ : ከምሉዕ ፋዉንዴሸን
3. ወ/ሮ ገነት ንጉሴ : ከቤቴል አዳማ ኦቲዝም ማዕከል
4. ወ/ሮ ኩለን ኢብራሂም : የኛ ልጆች ኦቲዝም ማህበር
5. አቶ ኤርሚያስ ሙላቱ፡ ከጤና ሚኒስቴር
6. አቶ ሲሳይ ሀይሉ: ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
7. ወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ተስፋዬ፡ ከሲቪል ማህበረሰቦች ድርጅት ባለስልጣን
8. ዶ/ር ዳዊት ዳንኤል ፡ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
9. ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ ፡ የኦቲዝም በጎ ፈቃድ አምባሳደር (ከነህሚያ ኦቲዝም ማዕከል)
10. ዶ/ር አብዱልዋሃድ አሊ፡ ወላጅ
11. ወ/ሮ ልያ ተስፋዬ ፡ ወላጅ
12. ዶ/ር አሊ ሰኒ ፡ ከአካዳሚያ (አማካሪ)
13. ረ/ፕ ሄኖክ ሀይሉ ፡ ከአካዳሚያ (ከአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ) ናቸው
ይህ ለሀገራችን ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ዜና ነው። የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ መመስረት በኦቲዝም ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማትን፣ ባለሙያዎችን እና ወላጆችን በአንድ ጥላ ስር በማምጣት የተበታተነውን ጥረት ወደ ላቀ ውጤት እንደሚያሸጋግረው ጥርጥር የለውም።
የተመረጡት የቦርድ አባላት ስብጥርም ከመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ከሲቪል ማህበረሰብ፣ ከሚዲያ፣ ከምሁራን እና ከራሳቸው ከወላጆች መሆኑ ሶሳይቲው ሁሉን አቀፍ እውቀትና ድጋፍ እንዲኖረው ያደርገዋል።
የዚህ ሶሳይቲ መመስረት የሚኖረው ዋና ዋና ጥቅሞች፦
የፖሊሲ ተፅዕኖ ማሳረፍ፦ በኦቲዝም ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመንግስት አካላት በአንድ ድምፅ በማቅረብ የተሻሉ ህጎች እና መመሪያዎች እንዲወጡ ማድረግ።
ግንዛቤ መፍጠር፦ በህብረተሰቡ ዘንድ ስላለው የተሳሳተ አመለካከት በሰፊውና በሳይንሳዊ መንገድ መስራት።
ልምድ ልውውጥ፦ የተለያዩ ማዕከላትና ባለሙያዎች ያላቸውን ምርጥ ተሞክሮ እንዲለዋወጡ መንገድ መክፈት።
ለወላጆች ድጋፍ፦ ወላጆች መረጃ የሚያገኙበትና እርስ በእርስ የሚደጋገፉበት ጠንካራ መድረክ መፍጠር።
ኒያ ፋውንዴሽን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እያለ ለማለት ለተመረጡት የቦርድ አባላትም ይህን ትልቅ አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ብርታቱንና ስኬቱን ይመኝላቸዋል።













