Events
ስለ ኦቲዝም ልጆች ፍቅር እንጓዛለን!
በደቡብ ኢትዮጵያ መዲና በዎላይታ ሶዶ ከተማ!
አርብ ግንቦት 16/ 2016 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ማዕከል ዎላይታ ሶዶ “ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው የማህበረሰቡን ፍቅር፣ መረዳት፣ እንክብካቤ እና ድጋፍ ይሻሉ!” በሚል መሪ ቃል የእግር ጉዞ እናደርጋለን!
የደቡብ ኢትዮጵያዋ የህብረ ብሄራዊነት ፈርጥ #ዎላይታ_ሶዶ እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጁ ሆናለች!
ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ የኦቲዝም ልጆች እና ወላጆች፣ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ መያዶች፣ ማህበራት፣ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች፣
ኒያ ፋውንዴሽን ከጤና ሚኒስቴር ፣ ዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር እና ልባም ኦቲዝም ማዕከል ጋር በመተባበር!
ቀን፦ አርብ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፦ ከሀይሌ ሪዞርት እስከ ሰርክል አደባባይ
#ስለ ኦቲዝም ያገባናል!











