News
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ የመጀመሪያውን የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ በትናንትናው ዕለት ( 14/5/2018) የተደረገ ሲሆን በማድረግ፣ ማህበሩን አደረጃጀት ለማጠናከር እና ህጋዊ ሰዉነት ለማግኘት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች እንዲሁም ከአጭር እና ረጅም ግዜ አኳያ መሰራት በሚገቡ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
የቦርድ አባላትና የስራ ድልድል አስመልክቶ ፡ ሶሳይቲው የኢትዮጵያን አገር አቀፍ የኦቲዝም ዘርፍ በብቃት ለመምራት ሀሉም የዳይሬክሮች ቦርድ አባላት ከፍተኛ ሀላፊነት የሚጠበቅ ሲሆን የሚከተሉትን የሃላፊነት ጉዳዮችን በመለየት ምደባዎችን አድርጓል።
በዚህም መሰረት፣
1. ወ/ሮ እሌኒ ዳምጠው – ሰብሳቢ
2. ወ/ሮ ትዕግስት ሀይሉ – ም/ሰብሳቢ
3. አቶ መንግስቱ ወልዴ – ጸሃፊ፣
4. የተከበሩ ዶ/ር ታደለ ጩማሮ – ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት – የፌዴራል እና ፖሊሲ ጉዳዮች አስተባባሪ፣
5. ዶ/ር አሊ ሳኒ – የቴክኒካል እና ሙያዊ ጉዳዮች አስተባባሪ፣
5. ዶ/ር ዳዊት ዳንኤል – የክልሎች ጉዳይ አስተባባሪ፣
6. ጋዜጤኛ መላኩ ብርሃኑ – የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ጉዳዮች አስተባባሪ፣
7. ወ/ሮ ልያ ተስፋዬ – የስልጠናዎች እና ካዉንስሊንግ ጉዳይ አስተባባሪ፣
8. ወ/ሮ ራሄል አባይነህ – የወላጆች ጉዳይ አስተባባሪ፣
8. አቶ ኤርሚያስ ሙላቱ- ከጤና ሚኒስቴር – አባል
9. አቶ ሲሳይ ጥላሁን – ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር – አባል
10. አቶ ሄኖክ ሀይሉ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ – አባል
11. ዶ/ር አብዱልዋሃድ አሊ- ከወላጅ- አባል
12. ወ/ሮ መሰረት በቀለ – ከትምህርት ሚ/ር – አባል አባል
13. ወ/ሮ እምዬ ቢተው- ከስራ እና ክሎት ሚ/ር – አባል
15. ወ/ሮ ገነት ንጉሴ – አባል
16. ወ/ሮ ኩለን ኢብራሂም- አባል
17. ወ/ሮ ጥሩወርቅ ተስፋዬ- ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን – የአደረጃጀት ጉዳይ አማካሪ አድርጎ ሰይሟል።
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ የመጀመሪያውን የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ በትናንትናው ዕለት ( 14/5/2018) የተደረገ ሲሆን በማድረግ፣ ማህበሩን አደረጃጀት ለማጠናከር እና ህጋዊ ሰዉነት ለማግኘት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች እንዲሁም ከአጭር እና ረጅም ግዜ አኳያ መሰራት በሚገቡ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
የቦርድ አባላትና የስራ ድልድል አስመልክቶ ፡ ሶሳይቲው የኢትዮጵያን አገር አቀፍ የኦቲዝም ዘርፍ በብቃት ለመምራት ሀሉም የዳይሬክሮች ቦርድ አባላት ከፍተኛ ሀላፊነት የሚጠበቅ ሲሆን የሚከተሉትን የሃላፊነት ጉዳዮችን በመለየት ምደባዎችን አድርጓል።
• ሶሳይቲው በኒያ ፋዉንዴሸን (Nia Foundation) ውስጥ በጊዜያዊነት ቢሮ እንዲኖረው።
• ሶሳይቲው ህጋዊ ሰውነት በአስቸኳይ አግኝቶ ስራውን እንዲያከናዉን አስፈላጊው የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው ፣ የመመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ሰነዶች ፣ የቦርድ አባላት ተግባር እና ሃላፊት (Job Description) ሰነዶች ተጠናቀው ለቀጣይ ስብሳባ እንዲቀርብ እና ጸድቀው ወደ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከማመልከቻ ጋር ጥያቄ እንዲቀርብ፣
• በኢትዮጵያ በኦቲዝም ላይ የሚሰሩ ሁሉም ተቋማትና ድርጅቶች እንዲሁም ቤተሰቦች፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና አጋሮች በጋራ በመሆን የኦቲዝም ተሟጋቾችን ድምጽ ከፍ ለማድረግ መጪውን ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ወር (April 2026) በልዩ ሁኔታ በጋራ ለማክበር ተወስኗል። በዚህም መሠረት፡ April 2/2026 – የኢትዮጵያ የኦቲዝም ግንዛቤ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በደማቅ ሁኔታ በጋራ ለማክበር እና የመጀመሪያው “Ethiopian Autism Summit- 2026 ” ዝርዝር ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ ለቦርዱ እንዲቀርብ ።
• የሶሳይቲው አባላት ማፍራት ላይ በክልል የሚገኙ ድርጅቶች እና ቤተሰቦች ተደራሸ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ እና አባላት የሶሳይቲው አባል በመሆናቸው የሚያገኙት ጥቅሞች ላይ ዝርዝሩ ታይቶ የመመስረቻ ሰነዱ አካል እንዲሆን፣
• የተቋማት እና የኦቲዝም ማዕከላት በመዘዋወር ጉብኝት ማድረግ የሚገኙበትን ሁኔታ የአገልግሎት ደረጃቸውን፣ የልምድ ልዉዉጥ እንዲደረግ እና ማበረታታት እንዲቻል በተከታታይ እንዲደረግ ፕሮግራም እንዲወጣ እና ለቦርዱ እንዲቀርብ፣
• የሶሳይቲው የብራንዲንግ እና የሎጎ ዲዛይን፣ የዌብሳይት ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮች የኢትዮጵያን ኦቲዝም ሁኔታ እና የጋራ ድምጻችንን ማመላከት በሚችል መልኩ በጥንቃቄ እንዲሰሩ ሙያዊ እገዛም እንዲደረግ፣ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል።
ቀጣይ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ ፣
አርብ (ጃንዋሪ 30/2026) ከጠዋቱ 5:00-6:00 በኒያ ፋዉንዴሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲደረግ ቀጠሮ ተይዟል።
አብረን በመስራት ፣ ለኦቲዝም ልጆቻችንና ለቤተሰቦቻቸው የተሻለች ኢትዮጵያን እንፈጥራለን!
እናመሰግናለን!











