የእናት ባንክ የትንሣኤ በዓል በጆይ ኦቲዝም ማዕከል
የእናት ባንክ ኮርፖሬት ሰርቪስ ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ገነት ሀጎስ፣ የእናት ባንክ መምሪያ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ “ከእናት በላይ ማን” “የኦቲዝም ልጆች እናቶች የምንግዜም ጀግኖቻችን” በኒያ ፋዉንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል ከኦቲዝም ልጆች እና ወላጆቻቸው ጋር ደማቅ የበዓል ፕሮግራም አካሂደዋል።
“ከእናት በላይ ማን” “የኦቲዝም ልጆች እናቶች የምንግዜም ጀግኖቻችን ናቸው!”
#Ethiopia | የእናት ባንክ ኮርፖሬት ሰርቪስ ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ገነት ሀጎስ፣ የእናት ባንክ መምሪያ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ “ከእናት በላይ ማን” “የኦቲዝም ልጆች እናቶች የምንግዜም ጀግኖቻችን” በኒያ ፋዉንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል ከኦቲዝም ልጆች እና ወላጆቻቸው ጋር ደማቅ የበዓል ፕሮግራም አካሂደዋል።
ዘንደሮ ለ16 ተኛ የአፕሪል ወር ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ በመከበር ላይ ሲሆን ኒያ ፋዉንዴሽን ለ22 ተኛ ግዜ በአዲስ አበባ እና በትግራይ እና በድሬዳዋ ከተሞች የኦቲዝም ግንዛቤ ፕሮግራሞች በማዘጋጀት የማህበሰቡን ግንዛቤ የማዳበር ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት በማጠናቀቂያው አፕሪል 30 ደግሞ በጆይ ኦቲዝም ማዕከል መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ደማቅ የዋዜማ የበዓል ዝግጅት እና የኦቲዝም ግንዛቤ እንዲሁም የበዓል ስጦታ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ ላይ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እሌኒ ዳምጠው አስፋው የትንሳኤን በዓል ዋዜማ ልጆቻችንን እና ቤተሰቦችን በማለት አስበው ይህንን ያማረ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ያሰበውን እና በተግባር ያሳየውን የእናት ባንክ መላውን የባንኩን አመራር እና ሰራተኞች በኒያ ፋዉንዴሽን ስም እና በእናቶች ስም ያመሰገኑ ሲሆን ከኦቲዝም ጋር ያሉ ሰዎች አሁንም በርካታ ችግሮች የሚያጋጥማቸው፣ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ በቤት ዉስጥ ተዘግቶባቸው የሚያለቅሱ በርካታ ልጆች፣ እናቶች እና ቤተሰቦች በዘሚ የተጀመረውን ብርሃን እንዲያዩ ከጨለማ ለማውጣት ኒያ ፋዉንዴሽን በመስራት ላይ የሚገኙ በርካታ ስራዎች ጎን በመቆም አጋር በመሆን የባንኩ የጀመረው አስደሳች ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የእለቱ ክብር እንግዳ ጨምሮ የእናት ባንክ መምሪያ ዳይሬክተሮች የማዕከሉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና የኦቲዝም ድጋፍ ቴራፒዎች ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ መልዕክት ያስተላለፉት የዕለቱ የክብር እንግዳ ፤ የእናት ባንክ ኮርፖሬት ሰርቪስ ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ ገነት ሀጎስ በዚህ ማዕከል መገኘት ልዩ ስሜትን የሚፈጥር የሰው ተኮር እና ሰብአዊነት ስራ ለማየት ትክክለኛ ቦታ በመሆኑ በዚህ ልዪ ቀን ጆይ በመገኘታቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውንበመግለጽ እናት ባንክ በተለይም ሴት ጀግና ኢትዮጵያን ለአገራቸው የሰሩትን ተምሳሌታዊ ስራዎች የሚዘክር እንደመሆኑ በኦቲዝም ዙሪያ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም በመሆን “ጀግኒት” ሆነው ላለፉት ዘሚ የኑስ ማስታወሻ የሚሆን ቅርንጫፍ ፊጋ አካባቢ በመክፈት እውቅና በመስጠታቸው ክብር እንደሚሰማቸው ገልጸዋል። ወደፊትም የኦቲዝም እናቶችን እና ሴቶች ማብቃት ላይ ስልጠናዎችን በመስጠት ብድሮችን በማመቻቸት እንዲሁም ኒያ ፋዉንዴሽን ስራዎች ለማገዝ የሚሰሩ ሌሎች የማህበራዊ ሃላፊነት ስራዎች ላይ በሰፊው ለመስራት ዕቅድ ያለ መሆኑን በማረጋገጥ ከድርጅቱ ጎን መሆናቸውን አብስረዋል።
በፕሮግራሙ ላይ እናት ባንክ የኒያ ፋውንዴሽን ስራዎች ለማገዝ የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ ለኒያ ፋዉንዴሽን ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሳራ ሀሰን ያበረከቱ ሲሆን በጆይ ኦቲዝም በማዕከል ላሉ ልጆች፣ ወላጆች እና ሰራተኞች የትንሳኤ በዓል ዋዜማ አስመልከቶ የምሳ ግብዣ እንዲሁም በማዕከሉ ድጋፍ ለሚደረግላቸው 20 ወላጆች ደግሞ ልዪ የበዓል ስጦታ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 10 ኪሎ ዱቄት ፣ 5 ሊትር ዘይት እና የ1500 ብር የገንዘብ ድጋፍ አበርክተዋል።
በማጠናቀቂያውም ኒያ ፋዉንዴሽን ለእናት ባንክ በማዕከሉ ልጆች የተሰራ ስጦታ ያበረከተ ሲሆን ፋውንዴሽኑ በማስገንባት ላይ የሚገኘውን የኦቲዝም ልህቀት ማዕከል ለመደገፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በ9616 አጭር የመልዕክት ፅሁፍ ላይ ok ብሎ በመላክ እንዲሁም በቴሌ ብር 9616 ላይ፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሳር ቤት ቅርንጫፍ፣ በኒያ ፋውንዴሽን የአካውንት ቁጥር 1000066285808 ላይ ፋውንዴሽኑን በመደገፍ አገራዊ ሀላፊነቱን ይወጣ ዘንድ ጥሪ ተላልፏል።
በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የሚታፈቀውና ለብዙዎች ስራ ፈጣሪ የሆነው ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ለድርጅቱ 100,000 ሺ ድጋፍ አድርገዋል።
Nia Foundation #autismawareness











